ለዲስትሪክቱ ነዋሪዎች የፍትሐብሔር ህግ አገልግሎቶችን ማሳደግ
|
ለዲስትሪክቱ ነዋሪዎች የፍትሐብሔር ህግ አገልግሎቶችን ማሳደግ
የማህበረሰብ የዳሰሳ ጥናት
DC Courts [የዲሲ ፍርድ ቤቶች] የዲስትሪክቱ ነዋሪዎች ያለባቸውን የፍትሐብሔር ህግ ችግሮች ላይ የተሻለ ተጨማሪ የህግ እገዛ ማግኘት የሚችሉባቸውን የተለያዩ መንገዶችን የሚመለከት የፍትሐብሄር ህግ ቁጥጥር ማሻሻያ ግብረኋይል እንዲቋቋም አድርጓል። የፍትሐብሔር ህግ ችግሮች የወንጀል ነክ የህግ ጉዳዮች አይደሉም። “የፍትሐብሔር” ህግ ችግሮች ተብለው የሚጠቀሱት እንደ መኖሪያ ቤት/ከቤት የማስለቀቅ፣ ከጥቃት/ከቤት ውስጥ ጥቃት ጥበቃ ማድረግ፣ ልክ እንደ የልጅ አሳዳጊነት መብት እና የልጅ ማሳደጊያ የቀለብ መስጠት የመሳሳሉ የቤተሰብ ችግሮች፣ እና ልክ የህዝብ ጥቅምጥቅሞች እና ዕዳ የመሳሰሉ የገንዘብ ነክ የህግ ጉዳዮች ናቸው።
ግብረኋይሉ የተወሰነ ኋይነት የህግ አገልግሎቶችን ለመስጠት እንዲቻል፣ ጠበቃ ያልሆኑ፣ የሰለጠኑ ሰዎችን መጠቀም በተመለከተ የእናንተን አስተያየት ለመቀበል ይፈልጋል። እነዚህ የሚሰጡት አገልግሎቶች ሊያካትቱ የሚችሉት የህግ ምክር መስጠት፣ የህግ ሰነዶችን ማዘጋጀት እና መሙላት፣ የግልግል ወይም የሽምግልና ሂደት ላይ ሰዎችን ማገዝ እና የፍርድ ቤት ችሎት ቀን ላይ ማገዝ የመሳሰሉት ናቸው።
እነዚህ የሰለጠኑት ሰዎች ከተለመደው የጠበቃ ክፍያ ተመን በታች ክፍያ ሊያስከፍሉ ወይም የብቁነት መስፈርቱን ለሚያሟሉ ሰዎች ነፃ አገልግሎትን ከሚሰጡ የሙያ ፈቃድ ካላቸው ጠበቆች ወይም የህግ ማማከር አገልግሎት ሰጪ ድርጅት ጋር በጋራ ሊሰሩ ይችላሉ። እባክዎን የእርስዎን የፍትሐብሔር ህግ እገዛ ፍላጎት በተመለከተ ከታች የተጠቀሱትን ጥያቄዎች ለመመለስ ጥቂት ጊዜ ይውሰዱ። የዳሰሳ ጥናቱ ለማጠናቀቅ ከአምስት(5) ደቂቃ በታች ጊዜ ይወስዳል፣ እና የሚሰጡት ምላሽ ማንነትዎ በማይታወቅበት መልክ ይቀመጣል።
ስለ የፍትሐብሄር ህግ ቁጥጥር ማሻሻያ ግብረኋይል በተመለከተ የበለጠ መረጃ ለማግኘት ይሄንን አገናኝ ይጫኑ፦ https://www.dccourts.gov/about/civil-legal-regulatory-task-force
ስለ ተሳትፎዎት እናመሰግናለን!