2027 የሕግ ቅድሚያዎች፡ አስተያየትዎ ዋጋ አለው!

የአካል ጉዳተኝነትና የቅድመ-ልጅነት ድጋፎች ክፍል (DDECSD)

ይህ የዳሰሳ ጥናት ህግ አውጪዎች በ2027 የስብሰባ ወቅት ትኩረት ሊያደርጉባቸው ይገባል ብለው የሚያስቧቸውን ጉዳዮች እንዲያካፍሉ የተሰጠዎት ዕድል ነው።
 
አንድ ጉዳይ ሕግ እንዲወጣለት የሚያደርገው ምንድን ነው?
• ለውጦችን ለማድረግ ሕጎች ወይም የመንግስት የገንዘብ ድጋፍ ሊፈልጉ የሚችሉ ጉዳዮች።
 
አንድን ጉዳይ አስተዳደራዊ የሚያደርገው ምንድን ነው?
በኪንግ ካዎንቲ ነዋሪዎች ላይ ተጽህኖ የሚኖራቸው ነገር ግን የሕጎች ለውጥ የማያስፈልጋቸው ጉዳዮች። ስለምናስተዳድራቸው አገልግሎቶች ከድረ-ገጻችን ላይ የበለጠ መረዳት ይችላሉ። https://kingcounty.gov/ddecsd 
 
የእርስዎን ግብረ-መልስ እንዴት እንደምንጠቀም፡
  1. • የሕግ አውጭ ግብረ-መልስ የኪንግ ካዎንቲ የአዕምሮና የአካል ጉዳተኞች ሕግ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉዳዮች ምን እንደሆኑ ለመወሰን ያግዘናል። እነዚህ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ነገሮች በ2026 መገባደጃ ላይ በዓመታዊ የህግ አውጭ መድረካችን ከህግ አውጪዎች ጋር ይጋራሉ።
  2. • አስተዳደራዊ ግብረ-መልስ ክትትል የምናደርግባቸውንፕሮግራሞች ለማስተዳደር ይረዳናል።
 
እንጀምር!