Screen Reader Mode Icon
ጥሩ የአመራር እድል።
King County Metro ለ Lynnwood Link Connections Mobility Board እየቀጠረ ነው። Lynnwood Link Connections በሰሜን ምዕራብ King County እና በደቡብ ምዕራብ Snohomish County የLink light rail አገልግሎት እስከ 2024 ድረስ በሚሰፋበት ጊዜ የመጓጓዣ ግንኙነቶችን ለማሻሻል የተቀናጀ ሂደት ነው። በሰሜን ምዕራብ King County፣ ደቡብ ምዕራብ Snohomish County እና አካባቢው የሚኖሩ፣ የሚሰሩ እና የሚጓዙ የማህበረሰብ አባላት ስለ አውቶቡስ አገልግሎት ዕቅዳችን እና ማህበረሰባችንን የማዳረስ ሂደት ለMetro እንዲያመለክቱ እና እንዲያማክሩ ይበረታታሉ እንዲሁም ምክሮች ለ፦  
  • የመጓጓዣ ተጠቃሚዎችን በሰሜን Seattle እና ዳውንታውን Lynnwood መካከል ወዳሉ 5 አዲስ የLink light rail ጣቢያዎች ማገናኘት። 
  • በ Link light rail የአውቶቡስ አገልግሎት ማባዛትን መቀነስ  
  • የመጓጓዣ አማራጮችን ማሻሻል፣ በተለይም በታሪክ ዝቅተኘ ስፍራ ለተሰጣቸው ቡድኖች 
  • በዕቅድ ሂደት ውስጥ አሁን ላይ ያሉትን እና ቁልፍ ደንበኞችን በእኩልነት ማሳወቅ፣ ማሳተፍ እና ማበረታታት 
  • ከ COVID-19 ማገገም ጋር የተያያዙ ሌሎች ካውንቲ አቀፍ የአገልግሎት ለውጦች ጋር አብሮ መስራት 
Metro በታሪክ ከመጓጓዣ ጋር በተያያዙ የውሳኔ ሰጭ ውይይቶች ቦታ ያልተሰጣቸው እና በእነዚህ ውሳኔዎች ቀላል የማይባል ተፅእኖ ያደረባቸውን የማህበረሰብ ክፍሎችን የሚወክል Mobility Board ለማቋቋም ያለመ ነው። እነዚህ የማህበረሰብ ክፍሎች ጥቁር፣ የሀገሩ ተወላጆችን እና ቀለም ያላቸውን ሰዎች፤ የአካል እና/ወይም የግንዛቤ እክል ያለባቸው ሰዎች፤ ከዝቅተኛ እስከ ምንም ገቢ የሌላቸው ሰዎች፤ ስደተኞች እና ጥገኞች፤ እንዲሁም በቋንቋ የተለያዩ ማህበረሰቦችን ያካትታል። እንዲሁም በዕድሜ የገፉ አዛውንቶችን፣ ተማሪዎችን እና ወጣቶችን እንዲሁም በእነዚያ ቡድኖች ውስጥ Lesbian, Gay, Bisexual, Trans, Queer, Intersex, Asexual and others (LGBTQIA+፣ግብረ ሰዶማዊያን) በመባል የሚታወቁ ሰዎችን ውክልና እንፈልጋለን።

Mobility Board ማመልከቻዎችን እስከ ማርች 31፣ 2022 ድረስ እየተቀበሉ ነው።

ትክክለኛ የግንኙነት መረጃ የሚያቀርቡ ሁሉም አመልካቾች ስለ ምርጫ ውሳኔ ኤፕሪል መጀመሪያ ላይ ይነገራቸዋል። የመጀመሪያዎቹ ስብሰባዎች የሚከናወኑት በኤፕሪል መጨረሻ እና/ወይም በሜይ 2022 መጀመሪያ ላይ የሚሆን ሲሆን ትክክለኘው ቀን በቦርድ አባላት ተገኝነት ላይ የሚመሰረት ይሆናል።

ይህን ማመልከቻ ለማጠናቀቅ 15 ደቂቃ ያህል ይወስዳል። ማንኛውም አይነት ጥያቄዎች ካልዎት ወይም ይህ ማመልከቻ በኢሜይል እንዲላክልዎ ወይም በፖስታ እንዲላክልዎ ከፈለጉ እባክዎ Metro በ haveasay@kingcounty.gov ወይም (206) 263-1939 ያነጋግሩ።
0 of 15 answered
 

T