መግቢያ

ይህን ጥናት በሚከተሉት ቋንቋዎችም ማግኘት ይቻላል

English

Français
Tagalog
日本の

ለምን ይህን ጥናት መውሰድ አስፈለገ?

የባንፍ ከተማ፣ የካንሞር ከተማ እንዲሁም በየዘርፉ ያሉ ሌሎች አያሌ አካባቢያዊ ድርጅቶች የጋራ ስልቶችን በመቀየስ ሁላችንም በቦው ቫሊ ያለን ሰዎች

-              የተቀባይነት እና የግንኙነት ስሜት እንዲሰማን

-              አባል እንደሆንን እንድናውቅ

-              ጤናማ እንድንሆን

-              የአገልግሎቶችና እድሎች ተጠቃሚ እንድንሆን

-              በማኅበረሰባዊ ኑሮ ላይ ተካፋይ እንድንሆን

ተባብረው በመስራት ላይ ይገኛሉ።

ግባችን ቦው ቫሊ ሁሉም ሰው የሚሳተፍበት፣ የሚያበረክትበት እና በደህና የሚኖርበት ስፍራ እንዲሆን ማድረግ ነው።

ይህ ጥናት ከካናዳ ውጭ የተወለዱት የቦው ቫሊ ነዋሪዎች ካናዳ ውስጥ ከተወለዱት ነዋሪዎች የተለየ ተሞክሮዎች በቦው ቫሊ ይኖሯቸው ከሆነ ለመረዳት ይጠቅመናል። ከ4 የቦው ቫሊ ነዋሪዎች አንዱ ከካናዳ ውጭ የተወለደ ነው።

ምን ያክል ይፈጃል?

ከ15-30 ደቂቃዎች። ጥናቱን በስልክም 403-431-0705 ላይ ከሰኞ እስከ አርብ ከ8:30am – 5:00pm በመደወል መካፈል ይችላሉ።

ማንን ይመለከታል?

ይህንን ጥናት በባንፍ፣ ካንሞር፣ ሌክ ሉዊዝ፣ ኤክሻው፣ ሃርቪ ሃይትስ፣ ዴድ ማንስ ፍላትስ፣ ላክ ዴ አርክስ፣ ወይም ካናናስኪስ የሚኖሩ ከሆነ መውሰድ ይኖርብዎታል። ምን ያክል ግዜ እዚህ መኖርዎ ወይም ዜጋ ፣ ቋሚ ነዋሪ ወይም ግዜያዊ የውጭ ሰራተኛ መሆንዎ ምንም ፋይዳ የለውም። አሁን እዚህ እየኖሩ ከሆነ፥ ይህ ጥናት ለእርስዎ ነው።

ለምን ጥቅም ይውላል?

ማንነትዎንና ግላዊነትዎን እንጠብቅልዎታለን። በዚህ ጥናት የሚሰበሰበው መረጃ በአልበርታ የመረጃ ነጻነትና ግላዊነት መጠበቅያ ህግ ላይ በተደነገገው መሰረት ጥቅም ላይ የሚውል ነው። የማንነትዎን ሚስጥራዊነት ለመጠበቅ ሲባል መረጃዎችን ሪፖርት የምናደርገው ከሌሎች ሰዎች መረጃ ጋር አንድ ላይ በማቀላቀል ይሆናል።

የዚህ ጥናት ውጤቶች ከምንሰበስባቸው አያሌ መረጃዎች ጥቂቶቹ ናቸው። ሁሉንም የምንሰበስባቸውን መረጃዎች፥ የጥናቱን ውጤቶችም ጨምሮ፥ የ2019-2021 ኢንተግሬሽን ስትራቴጂን ለመፍጠር የማኅበረሰቡን እርዳታ ስንጠይቅ የምናጋራ ይሆናል።

የ2014 ምርምር እንዴት ጥቅም ላይ እንደዋለ ለማወቅ የሚከተለውን ድረ-ገጽ ይጎብኙ

http://www.bvipartnership.com/integration-strategy

ተጨማሪ መረጃ፡

ይህ ጥናት የሚሰጠው ሁሉም ነዋሪዎች በቦው ቫሊ እንዲሳተፉ፣ እንዲያበረክቱ፣ እናም እንዲያድጉ ለመርዳት በሚጥረው በማኅበረሰብ-አቀፍ ትብብራዊ ንቅናቄ በቦው ቫሊ ኢሚግሬሽን ፓርትነርሺፕ (BVIP) ነው። አባላቶቻችን የባንፍ ከተማ፣ የካንሞር ከተማ፣ አልበርታ ፓርክስ፣ ባንፍ ሌክ ሉዊዝ ሆስፒታሊቲ አሶሲዬሽን፣ ባንፍ ሚኒስቴሪያል አሶሲዬሽን፣ ቦው ቫሊ ኮሌጅ፣ ቦው ጃሊ ፕራይሜሪ ኬር ኔትወርክ፣ ክኔዲያን ሮኪስ ፐብሊክ ስኩልስ፣ ካንሞር ሆቴል ኤንድ ሎጂንግ አሶሲዬሽን፣ ጆብ ሪሶርስ ሴንትር፣ ፓርክስ ካናዳ፣ ሴትልመንት ሰርቪስስ ኢን ዘ ቦው ቫሊ፣ እና ሌሎችም ናቸው። ግለሰቦችም (12 አባላት ያሉትን ኢሚግራንት አድቫይዘሪ ግሩፕ ጨምሮ) ሜምበርሺፑን በበጎ ፈቃደኝነት ያገለግላሉ።

BVIP በኢሚግሬሽን፣ ሬፊዩጂስ ኤንድ ሲቲዝንሺፕ ካናዳ ፈንድ የሚደረግ ነው።

ለበለጠ መረጃ www.bvipartnership.com ይጎብኙ

ጥያቄ አለዎት?

በ bvip@banff.ca ወይም 403-431-0705 ያግኙን።

በዚህ ጥናት ከተካተቱት ጥያቄዎች ውስጥ የትኛዎቹም ካስጨነቁዎት በባንፍ ሚኒራል ስፕሪንግስ ሆቴል እና ካንሞር ሆስፒታል በማንኛውም ቀን ከ2:00pm - 9:00pm እርዳታ ማግኘት ይችላሉ። ቀጠሮ አያስፈልግዎትም። ለስልክ እርዳታ በማንኛውም ሰዓት (በቀን 24 ሰዓት) የካልጋሪ ዲስትረስ ሴንትር 403.266.HELP (4357) ላይ መደወል ይችላሉ።

ስለ ግዜዎት እና ሃሳብዎትን ስላጋሩን እናመሰግናለን!

 

 
4% of survey complete.

T