ክፍል 2። እንኳን ደሕና መጡ

ንኡስ ክፍል 1

በ2018፣ ድምጽ ሰጪዎች የ APS ተማሪዎች ጤንነትና ደህንነት ላይ ያተኮረውን የአውሮራ የሕዝብ ት/ቤቶች (APS) ተጨማሪ ታክስ እንዲሰበስብ ያቀረበውን ሃሳብ አጽድቀዋል። ምስጋና ለአውሮራ ድምፅ ሰጪዎች ይሁንና፣ APS በአምስተኛ ክፍል ተማሪዎችና ቤተሰቦቻቸው አማካይነት ከ1000 በላይ ለሚሆኑ አፀደ ሕጻናት በ2019-20 የትምህርት ዘመን የድሕረ ት/ቤት ፕሮግራሞችን እንዲያገኙ ተደራሽነቱን ለማስፋት ችሏል።

APS የድሕረ ት/ቤት ፕሮግራም ማስፋፊያን ለመደገፍ ከ American Institutes for Research (AIR) ጋር እየሰራ ነው። የአውሮራ ማሀበረሰብን ፍላጎቶች በተሻለ ሁኔታ ለመረዳት፣ AIR በ APS የድሕረ ት/ቤት ማስፋፊያ የዳሰሳ ጥናተ አማካይነት ከቤተሰቦች፣ ከት/ቤት ርዕሳነ መምህራን፣ ከድሕረ ት/ቤት ፕሮግራም አቅራቢዎችና ከማህበረሰቡ አባላት መረጃ እየሰበሰበ ነው። የማህበረሰበ ግብዓት ለእኛ አስፈላጊ ነው፣ የእናንተንም ሃሳብ ለመስማት እንፈልጋለን!

የዳሰሳ ጥናቱን መሙላት ያለበት ማነው?

የዳሰሳ ጥናቱ በአውሮራ ማህበረሰብ ውስጥ ለሚኖር ማንኛውም ሰው ይቀርባል፤ ከቤተሰቦች እስከ የማህበረሰብ አባላት፣ የት/ቤት ርዕሳነ መምህራን፣ የድሕረ ት/ቤት ፕሮግራመ ዳይሬከተሮችና የድሕረ ት/ቤት ሳይት አስተባባሪዎች ይሳተፋሉ። በድሕረ ት/ቤት ፕሮግራሞች ውስጥ ቢሳተፉም ባይሳተፉም ይህን የዳሰሳ ጥናት መሙላት ይችላሉ። ይህ የዳሰሳ ጥናት ለሁሉም ሰው ክፍት ነው!

የዳሰሳ ጥናቱን ለመሙላት ምን ያህል ጊዜ ይወስድብኛል?

የዳሰሳ ጥናቱን ለመሙላተ በግምት ሦስት አስር ደቂቃ ይፈጃል። የዳሰሳ ጥናቱን አንዴ መሙላተ ከጀመሩ በኋላ መልሶችዎን አስቀምጠው በሌላ ጊዜ ተመልሰው ለመሙላት አይችሉም።  በተቻለዎት መጠን በርካታ ጥያቄዎችን ለመመለስ የቻሉትን ሁሉ እንደሚሞክሩ ተስፋችን ነው። 

ጠቀሜታዎችና ስጋቶች

ከዚህ የዳሰሳ ጥናት የሚሰበሰበው መረጃ AIR፣ APS፣ እና የ APS የድሕረ ት/ቤት ሲስተም አማካሪ ቡድን በእርስዎ፣ ግቦች፣ ምርጫዎችና ፍላጎቶች ላይ ተመስርተው ውሳኔዎችን እንዲወስኑ ያግዛቸዋል። እርስዎ የሚያጋሩት መረጃ በመላው ኮሙኒቲ ውስጥ በድሕረ ት/ቤት ፕሮግራሞች ውስጥ በአሁኑ ጊዜ ምን እየተካሄደ እንዳለ እንድንገነዘብም ያግዘናል። ይህም ድምፅዎ እንዲሰማ ዕድል የሚፈጥርልዎ ሲሆን ሃሳብዎትን እንደሚያጋሩንም ተስፋ እናደርጋለን። በዕለት ተዕለት ኑሮ ውስጥ ከሚያጋጥሙት ባሻገር በዚህ የዳሰሳ ጥናት ውስጥ መሳተፍ የሚያስከትላቸው የሚገመቱ ወይም የሚታወቁ ስጋቶች የሉም።

የዳሰሳ ጥናቱን የግድ መሙላት አለብኝ?

ይህ የዳሰሳ ጥናት በፈቃደኝነት ላየ የተመሰረተ ነው። ላለመሳተፍ ቢወስኑ ምንም ዓይነት ውጤት አያስከትልብዎትም። ለመሳተፍ ከወሰኑ፣ ማንኛውንም ጥያቄ መዝለል ወይም በማንኛውም ጊዜ የዳሰሳ ጥናቱን ማቆም የሚችሉ ሲሆን በዚህም ምክንያት ቅጣት አይኖርብዎትም።

ግላዊ መብትና የማቋረጥ ነጻነት

ለዳሰሳ ጥናቱ የሚሰጡት እያንዳንዱ መልስ ለ AIR ቡድን ብቻ ዝግጁ ይደረጋል፤ መረጃዎት ይፋ አይደረግም። ምላሾችዎ ከሌሎች መልሶች ጋር ተጠቃልለው ለ APS ሪፖርት ይደረጋሉ። ስምዎን በየትኛውም ሪፖርት ላይ አንጠቀምም። ተሳትፎ በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ነው፤ ተሳታፊዎችም ማንኛውንም ጥያቄ አለመመለሰ ይችላሉ። በዳሰሳ ጥናቱ ውስጥ መሳተፍዎ ልጅዎ በድሕረ ት/ቤት ፕሮግራሞች ውስጥ የሚኖረው ተሳትፎ ላይ የሚያስከትለው ውጤት የለም። የዳሰሳ ጥናቱን በተመለከተ ማንኛውም ጥያቄ ካለዎት፣ እባክዎ ለ Jill Young በስልክ ቁጥር 312-288-7635 ወይም በኢሜይል jiyoung@air.org ማሳወቅ ይችላሉ። የ APS የድሕረ ት/ቤት ስርዓትን በተመለከተ ለሚኖርዎት አጠቃላይ ጥያቄዎች፣ ለ Shannon Blackard በኢሜይል smblackard@aurorak12.org ወይም በስልክ ቁጥር 720-614-6478 ደውለው ያሳወቁ።

ተጨማሪ መረጃ
 ተሳታፊ በመሆንዎ ስላሉዎ መብቶች አሳሳቢ ጉዳዮች ወይም ጥያቄዎች ካሉዎ፣ እባክዎ የፕሮጄክት ተሳታፊዎችን ጥበቃ በተመለከተ ሃላፊነት ላለበት ለ AIR Institutional Review Board በኢሜይል IRB@air.org፣ ከክፍያ ነጻ በሆነው ስልክ ቁጥር 1-800-634-0797፣ ወይም c/o IRB, 1000 Thomas Jefferson St. NW, Washington, DC 20007 ያሳውቁ።

 

የዳሰሳ ጥናቱን ለመሙላት እፈልጋለሁ። በቀጣይ ምን አደርጋለሁ?

ከላይ የቀረበውን መረጃ ተገንዝበው በዚሀ የዳሰሳ ጥናት ውስጥ ለመሳተፍ ከተስማሙ፣ እባክዎ "አዎ፣ ለመቀጠል ተስማምቻለሁ" የሚለው አጠገብ ያለው ሳጥን ላይ ምልክት ያድርጉ።

የዳሰሳ ጥናቱን ለመሙላት ካልፈለጉ፣ እባክዎ "የለም፣ ለመቀጠል አልፈልግም" የሚለው አጠገብ ያለው ሳጥን ላይ ምልክት ያድርጉና ከዳሰሳ ጥናቱ ሲስተም ይወጣሉ።

Question Title

* 1. ይህን የዳሰሳ ጥናት ለመሙላት ተስማምተዋል?

T